<!DOCTYPE HTML PUBLIC "-//W3C//DTD HTML 4.01 Transitional//EN" "http://www.w3.org/TR/html4/loose.dtd"> <html DIR="LTR"> <head> <meta http-equiv="Content-Type" content="text/html; charset=UTF-8"> <link rel="icon" type="image/ico" href="/tools/dlpage/res/chrome/images/chrome-16.png"><title>የGoogle Chrome የአግልግሎት ስምምነት ውሎች </title> <style> body { font-family:Arial; font-size:13px; } h2 { font-size:1em; margin-top:0 } </style> <script type="text/javascript"> function carry_tracking(obj) { var s = '(\\?.*)'; var regex = new RegExp(s); var results = regex.exec(window.location.href); if (results != null) { obj.href = obj.href + results[1]; } else { s2 = 'intl/([^/]*)'; regex2 = new RegExp(s2); results2 = regex2.exec(window.location.href); if (results2 != null) { obj.href = obj.href + '?hl=' + results2[1]; } } } </script></head> <body> <h2>የGoogle Chrome የአግልግሎት ስምምነት ውሎች </h2> <p>እነዚህ ውሎች ለሚሰራ የGoogle Chrome ኮድ ስሪት ተግባራዊ ይሆናሉ። የGoogle Chrome ሶርስ ኮድ በክፍት ሶርስ (Open source) ሶፍተዌር የፈቃድ ስምምነት ስር በዚህ http://code.google.com/chromium/terms.html ይገኛሉ።</p> <p><strong>1. ከGoogle ጋር ያለዎት ግንኙነት</strong></p> <p>የGoogle ምርቶች፣ ሶፍትዌር፣ ግልጋሎቶች እና ድር ጣቢያዎች (በዚህ ሰነድ ውስጥ በአንድነት “ግልጋሎቶች” ተብለው የተጠቀሱት እና በተለየ የጽሁፍ ስምምነት ለርስዎ በGoogle አማካይነት ከቀረቡት ግልጋሎቶች ውጪ) በርስዎና በGoogle መካከል በሚደረግ ህጋዊ ስምምነት ለስምምነት ውሎቹ ተፈፃሚ ይሆናሉ። “Google” ማለት Google Inc. ማለት ሲሆን ዋናው የንግድ ቦታውም በ1600 Amphitheatre Parkway፣ Mountain View፣ CA 94043፣ ዩናይትድ ስቴትስ ነው። ይህ ሰነድ ስምምነቱ እንዴት እንደተዘጋጀ እና አንዳንድ የስምምነት ውሎች እንዴት ተፈፃሚ እንደሚሆኑ ይገልፃል።</p> <p>አልያም ከGoogle ጋር በጽሁፍ ስምምነት ካደረጉ፣ ከGoogle ጋር ያለዎት ስምምነት ቢያንስ በዚህ ሰነድ ውስጥ የተገለጹትን ውሎች እና አካሄዶች ሁልጊዜ የሚያካትት ይሆናል። እነዚህም “አለም አቀፍ ውሎች” ተብለው ከዚህ በታች ተጠቅሰዋል። የክፍት ሶርስ (Open source) ሶፍትዌር ፈቃዶች ለGoogle Chrome ሶርስ ኮድ የተለየ የጽሁፍ ስምምነቶች መስርተዋል። በተወሰነ መጠን የክፍት ሶርስ (Open source) ሶፍትዌር ፍቃዶች እነዚህን አለም አቀፍ ውሎች በግልጽ ይተካሉ፤ Google Chromeን ወይም በGoogle Chrome የተካተተን አንድ የተወሰነ አካል ስለመጠቀም ከGoogle ጋር ያለዎትን ስምምነት የክፍት ሶርስ (Open source) ፈቃዶች የሚያስተዳድሩት ይሆናል።</p> <p>1.3 ከGoogle ጋር ያለዎት ስምምነት በዚህ ሰነድ «መግለጫ ሀ» ውስጥ የተጠቀሱት ደንቦችና ሌሎች እነዚህ ግልጋሎቶች ላይ የሚውሉ የህግ መግለጫዎችና አለማቀፋዊ ውሎችን ይጠቅልላል። እነዚህ ሁሉ “ተጨማሪ ውሎች” በሚል ከዚህ በታች ተቀምጠዋል። ተጨማሪ ውሎች አንድ ግልጋሎት ላይ ተፈፃሚ ሲሆኑ፣ በግልጋሎቱ ውስጥ ወይም ግልጋሎቱን በሚጠቀሙበት ጊዜ እንዲያነቡት ይደረጋል። </p> <p>1.4 የአለምአቀፍ ውሎች እና ተጨማሪ ውሎች በአንድ ላይ ሆነው በርስዎና በGoogle መካከል ግልጋሎቶቹን ከመጠቀምዎ ጋር በተያያዘ በህግ የጸና ስምምነትን ይፈጥራሉ። እነዚህን ጊዜ ወስዶ በጥንቃቄ ማንበብ አስፈላጊ ነው። ይህ ህጋዊ ስምምነት ጠቅል ብሎ ከዚህ በታች “ውሎች” በሚል ተጠቅሷል።</p> <p>ተጨማሪ ውሎች በሚሉት እና አለምአቀፍ ውሎች በሚሉት መካከል የሚቃረኑ ነገሮች ካሉ፣ ከዛ ግልጋሎት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ውሎች የበላይነቱን የሚወስዱ ይሆናል።</p> <p><strong>2. ውሎችን መቀበል</strong></p> <p>ግልጋሎቶቹን ለመጠቀም በመጀመሪያ ከግልጋሎቶቹ መስማማት አለብዎ። ውሎቹን ካልተቀበሉ ግልጋሎቶቹን ላይጠቀሙ ይችሉ ይሆናል።</p> <p>ውሎቹን እንደሚከተለው መቀበል ይችላሉ፦</p> <p>(ሀ) በውሎቹ ለመስማማት ወይም ለመቀበል ጠቅ በማድረግ፣ በማንኛውም ግልጋሎት Google በሚኖረው የተጠቃሚ በይነገጽ ላይ ይህ አማራጭ ይገኛል፤ ወይም </p> <p>(ለ) ግልጋሎቶቹን ዝም ብለው በመጠቀም። በዚህ ሁኔታ ግልጋሎቶቹን መጠቀም ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ Google ወሎቹን ተረድተውና ተስማምተው እንደሆነ አድርጎ ይመለከተዋል።</p> <p><strong>3. የውሎቹ ቋንቋ</strong></p> <p>3.1 Google የውሎቹን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቅጂ ትርጉም ካቀረበልዎ፣ ትርጓሜው የቀረበው በርስዎ መቾት ብቻ መሆኑንና ከGoogle ጋር ያለዎትን ግንኙነት የውሎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቅጂ የሚያስተዳድረው መሆኑን ተስማምተዋል።</p> <p>3.2 በእንግሊዝኛ ቋንቋ ቅጂውና በትርጉም ቅጂው መካከል የውሎች መቃረን ቢኖር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቅጂው የበላይነቱን የሚወስድ ይሆናል።</p> <p><strong>4. የግልጋሎቶቹ ደንብ በGoogle</strong></p> <p>4.1 Google በአለም ላይ ህጋዊ ቅርንጫፎችና ሕጋዊ ተባባሪ ድርጅቶች አሉት (ቅርንጫፎችና ድርጅቶች)። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ኩባንያዎች Googleን በመወከል ግልጋሎቶችን ለርስዎ የሚያቀርቡ ይሆናል። ቅርንጫፎችና ተባባሪዎች ግልጋሎቶችን ለማቅረብ መብት የተሰጣቸው መሆናቸውን አረጋግጠው ተስማምተዋል። </p> <p>4.2 Google ምርጥ ሊሆኑ የሚችሉ ልምዶችን ለተጠቃሚዎቹ ለማቅረብ ሳያቋርጥ አዳዲስ ነገሮችን ይሰራል። Google የሚያቀርባቸውን ግልጋሎቶች ቅርጽና ተፈጥሮ ያለቅድመ ማስታወቂያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊቀይር እንደሚችል አረጋግጠው ተስማምተዋል።</p> <p>4.3 በማያቋርጥ የአዳዲስ ነገር ፈጠራዎቻችን ጋር በተያያዘ፣ Google ግልጋሎቶችን (ወይም በግልጋሎቶቹ በሚገኙ ማንኛውም ባህሪያት) ማቅረቡን ለርስዎ ወይም በአጣቃላይ ለተጠቃሚዎች በGoogle የብቻ ውሳኔ ያለቅድመ ማስታወቂያ ለሁልጊዜ ወይም ለጊዜው ሊያቆም እንደሚችል አረጋግጠው ተስማምተዋል። በማንኛውም ጊዜ ግልጋሎቶቹን መጠቀም ማቆም ይችላሉ። ይህንንም ሲያደርጉም ለGoogle ማሳወቅ ላያስፈልግዎ ይችላል።</p> <p>4.4 Google መለያዎን መድረስ እንዳይችሉ ከደረገ ግልጋሎቶቹን ከመጠቀም፣ የመለያዎን ዝርዝሮች ወይም ማናቸውም ፋይሎች ወይም በመለያዎ ያሉ ሌሎች ይዘቶችን ከመድረስ ሊያግድዎ እንደሚችል አረጋግጠው ተስማምተዋል።</p> <p><strong>5. </strong>የርስዎ ግልጋሎቶችን መጠቀም</p> <p>5.1 ርስዎ ግልጋሎቶቹን ሊጠቀሙ የሚችሉት (ሀ) ውሎቹ እና (ለ) ማንኛውም ስራ ላይ የወለ ህግ፣ ደንብ ወይም በአጠቃላይ ተቀባይነት ያላቸው ልምዶች ወይም በስልጣን ውስጥ ተገቢነት ያላቸው መመሪያዎች (ከዩናይትድ ስቴትስ ወይም ከሌላ የሚመለከታቸው ሀገሮች ጋር የመረጃ ወይም የሶፍትዌር ዝውውርን የተመለከቱ ህጎችን ጨምሮ) ለፈቀዷቸው አላማዎች ብቻ እንደሆነ ተስማምተዋል።</p> <p>5.2 ግልጋሎቶችን (ወይም አገልጋዮችን እና ከግልጋሎቶቹ ጋር የተገናኙ አውታረመረቦችን) ሊያሰናክል ወይብ ሊረብሽ ከሚችል ማንኛውም እንቃስቃሴ ውስጥ እንደማይሳተፉ ተስማምተወል።</p> <p>5.3 ርስዎ በተለየ ሁኔታ ከGoogle ጋር የተለየ ስምምነት በማድረግ ካልተፈቀደልዎ በስተቀር፣ ለማንኛውም አላማ ግልጋሎቶቹን እንደገና ማምረት፣ ማባዛት፣ መቅዳት፣ መሸጥ፣ ማሻገር፣ ወይም እንደገና መሸጥ እንደማይችሉ ተስማምተዋል። </p> <p>5.4 ማንኛውም በውሎች ስር ያሉትን ግዴታዎች ቢጥሱ እና ይህን ተከትሎ ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች (Googleን ሊጎዱ ለሚችሉ ማንኛውም ጥፋቶች) ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ (Google ለርስዎ ወይም ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን ጥፋት ማንኛውንም ኃላፊነት እንደማይወስድ) ተስማምተዋል።</p> <p><strong>6. ግላዊነት እና የርስዎ የግል መረጃ</strong></p> <p>6.1 የGoogleን የውሂብ አጠባበቅ ለሚመለከት መረጃ እባክዎን በhttp://www.google.com/privacy.html ያለውን የGoogle የግላዊነት ፖሊሲ ያንብቡ። ይህ ፖሊሲ ግልጋሎቶቹን ሲጠቀሙ Google የግል መረጃዎን እንዴት እንደሚይዝ፣ እና ግላዊነትዎን እንደሚጠብቅ ይገልፃል።</p> <p>6.2 የውሂብዎ አጠቃቀም በGoogle የግላዊነት ፖሊሲዎች መሰረት የሚካሄድ መሆኑን ተስማምተዋል።</p> <p><strong>7. በአገልግሎቶቹ ውስጥ ያሉ ይዘቶች</strong></p> <p>7.1 አገልግሎቶቹን በመጠቀመዎ ምክንያት ያገኟቸው መረጃዎች (እንደ ውሂብ ፋይሎች፣ የተጻፈ ጽሁፍ፣ የኮምፒውተር ሶፍትዌር፣ ሙዚቃ፣ የድምፅ ፋይሎች ወይም ሌላ ድምፆች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች ወይም ምስሎች) እነዚህ ይዘቶች ከመጡበት የመጀመሪያ ቦታ ያለው ሰው ላይ ሙሉ ኃላፊነት እንዳለ ተረድተዋል። እንደነዚህ ያሉ መረጃዎች ከታች እንደ “ይዘት” በሚል ተጠቅሰዋል። </p> <p>7.2 አንድ የአገልግሎቶቹ ክፍል ሆኖ ለርስዎ የቀረበ ይዘት በአገልግሎቶቹ ውስጥ ያለ ነገር ግን በአገልግሎቶቹ ውስጥ ላሉ ማስታወቂያዎች እና የተደገፈ ይዘት ብቻ ያልተወሰነ፣ ይህን የዘት ለGoogle ባቀረቡ ደጋፊዎች ወይም አስታዋቂዎች (ወይም እነርሱን ለሚወክሉ ሌሎች ሰዎች ወይም ኩባንያዎች) አእምሮአዋዊ ባለቤትነት የተጠበቀ መሆኑን ማወቅ አለብዎ። በGoogle ወይም በዛ ይዘት ባለቤቶች በተለየ ስምምነት ይህን እንዲያደርጉ በግል ካልተነገርዎ በስተቀር፣ ይህን ይዘት (በሙሉም ሆነ በከፊል) ማሻሻል፣ ማከራየት፣ በሊዝ መሸጥ፣ ማዋስ፣ መሸጥ፣ ማሰራጨት ወይም አውጣቶ/ወስዶ ስራዎችን መፍጠር አይችሉም።</p> <p>7.3 Google የማንኛውም አገልግሎትን ማንኛውም ወይም ሁሉንም ይዘት የቅድመ-ማጣራት፣ የመከለስ፣ የመለየት፣ የማጣራት፣ የማሻሻል፣ የመከልከል ወይም የማስወገድ መብትን (ያለምንም ግዴታ) ይጠብቃል። ለአንዳንድ አገልግሎቶች፣ Google ግልጽ የሆኑ የግብረ ስጋ ግንኙነት ይዘቶች ያላቸውን ለይቶ ለማውጣት መሳሪያዎችን ሊያቀርብ ይችላል። እነዚህ መሳሪያዎች የአስተማማኝ ፍለጋ/ሴፍሰርች አማራጭ ቅንጅቶችን ያካትታሉ (http://www.google.com/help/customize.html#safe ይመልከቱ)። ከዚህም በተጨማሪ በገበያ ላይ የሚገኙ የሚቃወሙዋቸውን ቁሳቁሶች ሊገድቡ የሚችሉ አገልግሎቶችና ሶፍትዌር አሉ።</p> <p>7.4 አገልግሎቶቹን በመጠቀምዎ ደስ የማይል፣ ነውረኛ ወይም የሚቃወሙት ይዘት ሊያጋጥምዎት ይችላል፣ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ አገልግሎቶቹን የሚጠቀሙት በራስዎ ኃላፊነት መሆኑን ተርድተዋል።</p> <p>7.5 አገልግሎቶቹን ሲጠቀሙ ለሚፈጥሩት፣ ለሚያስተላልፉት ወይም እንዲታይ ለሚያደርጉት ማንኛውንም ይዘትና በዚህም በሚወሰዱ እርምጃዎች ለሚከሰቱት ነገሮች (Google ሊደርሱበት የሚችሉ ማንኛውም ጥፋቶችን ወይም ጉዳቶችን ጨምሮ) ለብቻዎ ኃላፊነቱን ለመውሰድ ተስማምተዋል። (እንዲሁም Google ለርስዎ ወይም ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን ኃላፊነት አይወስድም)።</p> <p><strong>8. የንብረት ባለቤትነት መብቶች </strong></p> <p>8.1 በአገልግሎቶቹ ውስጥ የተካተቱ ማንኛውንም የአእምሮዋዊ ንብረት መብቶችን ጨምሮ (መብቶቹ ተመዝግበው የነበረ ቢሆንም ባይሆንም፣ እና እነዚህ መብቶች በአለም ዙሪያ በየትም ቦታ የሚገኙ ቢሆንም) ሁሉንም ህጋዊ መብትን፣ ርዕስ እና ለአገልግሎቶቹ ወይም በአገልግሎቶቹ ፍላጎት ላይ Google (የGoogle ፈቃድ ያላቸው) ባለቤት መሆናቸውን በማረጋገጥ ተስማምተዋል።</p> <p>8.2 ከGoogle በጽሁፍ ካልተስማሙ በስተቀር ማንኛውንም የGoogle የንግድ ስሞች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ አርማዎች፣ የጎራ ስሞች እና ሌላ የተለየ ልዩ አርማ ባህሪያትን ለመጠቀም የሚያስችል በውሎቹ ውስጥ መብት የሚሰጥዎት አንቀጽ የለም። </p> <p>8.3 የትኛውንም እነዚህን ልዩ ባሀሪያት ለመጠቀም ከGoogle ጋር በተለየ የጽሁፍ ስምምነት ግልጽ የሆነ መብት ከተሰጠዎት፣ እንደዚህ ያሉ ባህሪያትን የሚጠቀሙት ለስምምነቱ፣ ለማንኛውንም ሊሰሩ የሚችሉ የውሎቹ ደንቦች እና ከጊዜ ወደጊዜ ለሚሻሻሉት የGoogle አርማ ባህሪይ አጠቃቀም መመሪያዎች ተገዢ እንደሆኑ ተስማምተዋል። እነዚህ መመሪያዎች በመስመር ላይ በዚህ http://www.google.com/permissions/guidelines.html (Google ከጊዜ ወደጊዜ ለዚህ አላማ በሚያቀርበው ሌላ URL ላይ) ሊታዩ ይችላሉ።</p> <p>8.4 Google በእነዚህ ውሎች ስር ወይም ርስዎ አገልግሎቶቹን በመጠቀም በማንኛውም በሚያቀርቡት፣ በሚልኩት፣ በሚያስተላልፉት ወይም በሚያሳዩት እንዲሁም በዛ ይዘት የተካተቱ የአእምሮአዊ ባለቤትነት መብቶች (እነዚያ መብቶች የተመዘገቡም ሆነም አልሆነም፣ እና እነዚህ መብቶች በአለም ዙሪያ በየትኘውም ቦታ ያሉ ቢሆንም) ጨምሮ ላይ ከርስዎ (ወይም ከርስዎ ፍቃድ ከተሰጣቸው) ምንም መብት፣ ርዕስ ወይም ፍላጎት እንደማያገኝ አረጋግጦ ተስማምቷል። ከGoogle በጽሁፍ ካልተስማሙ በስተቀር እነዚያን መብቶች የመጠበቅና እነዚያን መብቶች የማስተግበር ኃላፊነት እንዳለብዎ እና Google ይህን ርሶዎን ወክሎ የማድረግ ግዴታ እንደሌለበት ተስማምተዋል።</p> <p>8.5 ማንኛውም በአገልግሎቶቹ ውሰጥ የተካተቱ ወይም ያሉ የንብረት ባለቤትነት መብቶችን (የቅጂ መብትና የንግድ ምልክት ማስታወቂያዎችን ጨምሮ) እንደማያስወግዱ፣ ግልጽ እንዳይሆን እንደማይጋርዱ ወይም እንደማይለውጡ ተስማመተዋል።</p> <p>8.6 ይህን እንዲያደርጉ ከGoogle በግልጽ በጽሁፍ ካልተፈቀደለዎ በስተቀር፣ አገልግሎቶቹን ሲጠቀሙ ምንም አይነት የንግድ ምልክት፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም፣ የማንኛውንም ኩባንያ ወይም ድርጅት አርማ በተመለከተ ለእነዚህ ምልክቶች፣ ስሞች ወይም አርማዎች ባለቤት ወይም ፍቃድ ያላቸው ተጠቃሚዎች ግራ መጋባትን ሊፈጥር ወይም እንዲፈጥር አድርገው እንዳይጠቀሙ ተስማምተዋል።</p> <p> ለሌላ ጥቅም ምንም አይነት ፍቃድ አይሰጥምም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪም እንደሚሰጥም አይጠቅስም። ተጨማሪ መረጃ ሊገኝ የሚችለው ከMPEG LA, L.L.C. ይህን እዩ HTTP://WWW.MPEGLA.COM. </p> <p><strong>9. ፍቃድ ከGoogle</strong></p> <p>9.1 Google ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ክፍል የቀረቡ (ከታች “ሶፍትዌር” ተብለው የተጠቀሱትን) ለመጠቀም Google የግል፣ አለምአቀፍ፣ ከባለመብት ክፍያ ነፃ፣ ሊመደብ የማይችል እና የግል የሆነ ፍቃድ ይሰጥዎታል። የዚህ ፍቃድ ብቸኛ አላማ በስምምነት ውሎቹ ላይ በተፈቀደው መሰረት ርስዎ በGoogle የቀረቡልዎትን አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ እና በሚያገኟቸው ጥቅሞች እንዲደሰቱ ነው። </p> <p>9.2 ክፍል 1.2 በተመለከተ፣ በህግ በግልጽ ካልተፈቀደ ወይም ካላስፈለገ በስተቀር ወይም ይህን እንዲያደርጉ በGoogle በጽሁፍ ካልተነገርዎ በስተቀር፣ ርስዎ መቅዳት፣ ማሻሻል፣ ከተሰራ ስራ ፈጥሮ ማውጣት፣ መዋቅሩን መመለስ፣ ማሳ ወይም ካልሆነ ደግሞ የሶፍትዌሩን ሌላ በዛ የሚገኝ ክፍል ሶርስ ኮድ ለማውጣት መሞከር (እና ለሌላ ሰውም ቢሆን ይህን እንዲያደርግ መፍቀድ) ላይችሉ ይችላሉ።</p> <p>9.3 ክፍል 1.2 በተመለከተ፣ ይህን እንዲያደርጉ ከGoogle የተለየ የጽሁፍ ፍቃድ ካልተሰጥዎት በስተቀር፣ ሶፍትዌሩን የመጠቀም መብቶችዎን ማዛወር (ወይም ፍቃደዎን በውክልና መስጠት)፣ ሶፍተዌሩን ለመጠቀም ባሉዎት መብቶች ላይ የደህንነት ጥበቃ ፍላጎትን መስጠት፣ ወይም ካልሆነ ደግሞ ሶፍትዌሩን ለመጠቀም ያልዎትን ማንኛውም የመብትዎን ክፍል ማሰተላለፍ ላይችሉ ይችላሉ።</p> <p><strong>10. የይዘት ፍቃድ ከርስዎ </strong></p> <p>10.1 የቅጂ መብትን እና በግልጋሎቶቹ ላይ/በኩል በሚያቀርቡት፣ በሚያሰቀምጡት ወይም በሚያሳዩት ይዘት ውስጥ ቀድመው የያዟቸውን ሌሎች መብቶች ይዘዋል።</p> <p><strong>11. የሶፍትዌር ማዘመኛዎች</strong></p> <p>11.1 የሚጠቀሙት ሶፍትዌር ከጊዜ ወደ ጊዜ ማዘመኛዎችን ከGoogle በቀጥታ ሊያወርድ እና ሊጭን ይችላል። እነዚህ ማዘመኛዎች የሚዘጋጁት አገልግሎቶቹን ለመሻሻል፣ ለማሳደግ እና የበለጠ ለማጎልበት ሲሆን፤ ስህተቶችን የማሰተካከል፣ ጥቅሞችን የማሳደግ፣ አዲስ የሶፍትዌር ሞጁል እና ሙሉ ለሙሉ አዲስ የሆኑ ስሪቶችን መልክ ሊይዙም ይችላሉ። አገልግሎቶቹን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ እነዚህን የመሳሰሉ ማዘመኛዎችን ለመቀበል ተስማምተዋል (እንዲሁም Google እነዚህን ለእርሶ እንዲያደርስ ፈቅደዋል)።</p> <p><strong>12. ከGoogle ጋር ያለዎትን ግንኙነት ማቆም </strong></p> <p>12.1 የስምምነት ውሎቹ ከታች እንደተወሰነው በርስዎ ወይም በGoogle እስካልተቋረጡ ድረስ መተግበር ይቀጥላሉ። </p> <p>12.2 Google በማንኛውም ጊዜ ከርስዎ ጋር ያለውን ህጋዊ ስምምነት ሊያቋርጥ የሚችለው፦</p> <p>(ሀ) የስምምነት ውሎቹን የትኛውንም ደንብ ከተላለፉ (ወይም ለማድረግ አስበው አለመሆኑን በግልፅ ቢሚያሳይ ሁኔታ ከተገበሩ ወይም የስምምነት ውሎቹን ደንቦች መተግበር ካልቻሉ)፤ ወይም </p> <p> (ለ) Google በህጉ መሰረት ይህን ማድረግ ካስፈለገው (ለምሳሌ፣ ለርስዎ የቀረበው የአገልግሎቶቹ ደንብ የተከለከለ ከሆነ)፤ ወይም </p> <p>(ሐ) Google አገልግሎቶቹን ለርስዎ ለማድረስ የተጠቀመበት አጋር ድርጅት ከGoogle ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያቋርጥ ወይም አገልግሎቶቹን ለርስዎ ማቅረብ ሲያቆም፤ ወይም </p> <p> (መ) Google ርስዎ በሚኖሩበት ከተማ ወይም አገልግሎቶቹን በሚጠቀሙበት ቦታ ግልጋሎቶቹን ከዚህ በኋላ ለተጠቃሚዎቹ ወደ አለማቅረብ ሲሸጋገር፣ ወይም </p> <p> (ሠ) በGoogle ለርስዎ የቀረበው የአገልግሎቶቹ ደንብ፣ በGoogle እይታ ከዚህ በኋላ በንግድ ላይ ሊቆይ የሚችል ካልሆነ ነው።</p> <p>12.3 በስምምነት ውሎቹ ክፍል 4 ስር ያሉትን የአገልግሎቶች ደንብ በተመለከተ በዚህ ንዑስ ክፍል ውስጥ የGoogleን መብቶች የሚያስተጓጉል ምንም ነገር የለም </p> <p>12.4 እነዚህ የስምምነት ውሎች ወደ መጨረሻው በሚመጡበት ጊዜ ሁሉም ህጋዊ መብቶች፣ ርስዎ እና Google ከግዴታዎች እና ኃላፊነቶች ያገኛቸኋቸው ትርፎች፣ ተገዢ ከሆኑባቸው (ወይም የስምምነት ውሎች እንዱተገበሩ በነበረበት ጊዜ እየደጉ የነበሩ ) ወይም ሳያቋርጥ እንዲቀጥሉ የተገለጹ፣ በዚህ ማብቂያ የሚስተጓጎሉ አይሆንም፣ እንዲሁም በአንቀጽ 19.7 ያሉ ደንቦች ለእነዚህን መብቶች፣ ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች ያለማቋረጥ እየተፈፀሙ ይቀጥላሉ። </p> <p><strong>13. ዋሰትናን መከልከል</strong></p> <p>13.1 ንዑስ ክፍል 13 እና 14ን ጨምሮ የተገለፁት የስምምነት ውሎች በህጋዊ መንገድ የተከለከሉ ወይም በሚተገበር ህግ የተገደቡ ጥፋቶች የGOOGLEን ዋስትና ወይም ኃላፊነት እንዳይከለከል ወይም ውስን እንዲሆነ ምንም ነገር አያደርገውም። አንዳንዳንድ ስልጣኖች በቸልተኝነት ለሚከሰቱ፣ ለሚቋረጥ ስምምነት ወይም ለሚቋረጥ የተጠቆመ ደንብ ፣ ወይም ለሚገጥም፣ ወይም ሰበብ ለሚያመጣው ጉዳት የተወሰነ ዋስትና ወይም ሁኔታ ወይም ገደብ ወይም ኃላፊነት እዳይከለከሉ አይፈቅድም። በዚህ መሰረት በህጋዊ መንገድ ብቻ የተገደቡ ደንቦች ለርስዎ ተግባራዊ ይሆኑና የእኛ ቆይታ በህግ በተፈቀደው የመጨረሻው መጠን የተገደበ ይሆናል።</p> <p>13.2 የርስዎ አገልግሎቶችን መጠቀም ሙሉ ኃላፊነት ወስደው እና አገልግሎቶቹ የቀረቡት አሁን "እንደሆኑት" እና "እንደሚገኙት" መሆኑን በሚገባ ተረድተው እና ተስማምተው ነው። </p> <p>13.3 በተለይ GOOGLE፣ የGOOGLE ቅርንጫፎች እና ተባባሪዎች እንዲሁም የGOOGLE ፍቃድ ሰጪዎች የሚከተሉትን ለርስዎ አይወክሉም ወይም ዋስትና አይሰጡም።</p> <p>(ሀ) አገልግሎቶቹን መጠቀምዎ ፍላጎትዎን የሚያሟላ ስለመሆኑ፣</p> <p>(ለ) አገልግሎቶቹን መጠቀምዎ የማያቋረጥ፣ ጊዜያዊ፣ የደህንነቱ የተጠበቀ ወይም ከስህተት የነፃ ስለመሆኑ፣</p> <p>(ሐ) አገልግሎቶቹን የመጠቀምዎ ውጤት የሆነ ማንኛውም የያዙት መረጃ ትክክል እና አስተማማኝ ስለመሆኑ፣</p> <p>(መ) ከአገልግሎቶች ክፍል ለርስዎ የቀረበ ማንኛውም ሶፍትዌር በሚጠቀሙበት እና በሚሰሩበት ጊዜ የሚያጋጥሙ ጉድለቶች ስለመስተካከላቸው። </p> <p>13.4 በማንኛውም ሁኔታ የወረደ ነገር ወይም አገልግሎቶቹን በመጠቀም ምክንያት የተገኘ ነገርን የሚተገብሩት በራስዎ ኃላፊነት እና ውሳኔ ሆኖ በኮምፒውተርዎ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ወይም እንዲህ አይነት ነገርን በማውረድ ለሚፈጠር የውሂብ ጥፋት ሙሉ ተጠያቂ ይሆናሉ። </p> <p>13.5 ከGOOGLE በአገልግሎቶቹ የተገኙ የቃል ወይም የፅሁፍ የሆነ፣ ምክር ወይም መረጃ በውሎቹ በግልፅ ያልተቀመጠ ማንኛውንም ዋስትና አይፈጥሩም። </p> <p>13.6 GOOGLE በመቀጠል የተገለፁ ወይም የተመለከቱ ሁሉንም ዋስትናዎች እና ማንኛውንም አይነት ሁኔታዎች፣ ነገር ግን በተመለከቱት ዋስትናዎች እና በሚሸጡ ሁኔታዎች ያልተወሰኑትን ጨምሮ፣ ለአንድ የተወሰነ አላማ እና ህግ ባለመጣስ ያለ ብቃትን በግልፅ ይሽራል። </p> <p><strong>14. የተጠያቂነት ገደብ</strong></p> <p>14.1 ከላይ በአንቀፅ 13.1 አጠቃላይ ደንቦችን በተመለከተ GOOGLE፣ የGOOGLE ቅርንጫፎች እና ተባባሪዎች እንዲሁም የGOOGLE ፍቃድ ሰጪዎች ለሚከተሉት ነገሮች ኃላፊነት እንደማይወስድ በግልፅ ተረድተው ተስማምተዋል። </p> <p>(ሀ) ማንኛውም ቀጥተኛ፣ ቀጥተኛ ያልሆኑ፣ ልዩ ክስተቶች ወይም እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ጉዳቶች እነዚህም በርስዎ ምክንያት የመጡ፣ ነገር ግን ምክንያታዊ እና በማንኛውም ተጠያቂነት ስር ያለ ፅንሰ ሀሳብ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህም የሚያጠቃልለው ይህ ነው ብቻ ብለን የማንገድበው ማንኛውም ትርፍ ማጣት(በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በራስ ላይ ጉዳት ማምጣት)፣ የማንኛውም የመልካም ዓላማ ወይም የንግድ ዝና ጥፋት፣ ማንኛውንም የርስዎ የውሂብ ጥፋት ፣ ነገሮችን ወይም አገልግሎቶችን ለመተካት የተገኘ ወጪ ወይም ሌላ ተጨባጭ ያልሆነ ጥፋት ፤</p> <p>(ለ) በርስዎ ምክንያት የመጣ ማንኛውም ጥፋት ወይም ጉዳት፣ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የመጡትንም ጥፋቶች እና ጉዳቶች ጨምሮ፦ </p> <p>(1) ርስዎ በሙሉነቱ፣ በትክክለኛነቱ ወይም የማንኛውም ማስታወቂያ መገኘቱ ላይ ማንኛውንም ያስቀምጡትን መተማመኛ ወይም በማንኛውም በርስዎ እና በአስተዋዋቂዎች መከከል ያለ ማንኛውም ግንኙነት ወይም ግብይት ምክንያቶች የሆነ ወይም በአገልግሎቶች ላይ የሚመጡ የደጋፊዎች ማስታወቂያ፤</p> <p>(2) ማንኛውም GOOGLE በአገልግሎቶቹ ላይ ሊያደርጋቸው በሚችለው ለውጦች ወይም ለማንኛውም የአገልግሎቶቹ ደንቦች (ወይም በአገልግሎቶቹ ውሰጥ ያለ ማንኛውም ባህሪ) ላይ ቋሚ ወይም ጊዜያዊ መቋረጦች ፤ </p> <p>(3) አገልግሎቶቹን በመጠቀምዎ ወይም ሲጠቀሙ፣ ማንኛውም ይዘት ወይም የተያዘ ወይም የተላለፈ ውሂብ መሰረዝ፣ ያለአግባብ መጠቀም ወይም ማስቀመጥ አለመቻል፤ </p> <p>(4) ለGOOGLE ትክክለኛ የመለያ መረጃ ማቅረብ አለመቻል፤ </p> <p>(5) የይለፍ ቃልዎን ወይም የመለያዎን ዝርዝር የተጠበቀ እና አስተማማኝ አድርጎ መያዝ አለመቻል፤ </p> <p>14.2 GOOGLE አስተያየት ተሰጥቶት ወይም እንደእዚህ ላሉ ጥፋቶች ሊሆን የሚል መነሻ የሚያውቅ ቢሆንም ባይሆንም ከላይ በአንቀፅ 14.1 GOOGLE ለርስዎ ያለውን የተጠያቂነት ገደቦች የሚተገበሩ ይሆናል። </p> <p><strong>15. የቅጂ መብት እና የንግድ ምልክት ፓሊሲዎች </strong></p> <p>15.1 ተግባራዊ ከሆኑ አለም አቀፍ የአእምሮዋዊ ንብረት ህግ ( በዩናይተድ ስቴትስ፣ Digital Millennium Copyright Actን ጨምሮ) ለሚቃረኑ የቅጂ መብት ጥሰትን ለሚደግፉ ማታወቂያዎች መልስ መስጠት እና ተደጋጋሚ ጥሰቶችን የፈጸሙ መለያዎች ማቋረጥ የGoogle ፖሊሲ ነው። Google ፖሊሲን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይገኛል http://www.google.com/dmca.html።</p> <p>15.2 የGoogleን የማስተዋወቅ ንግድ ጋር በተያያዘ Google የንግድ ምልከት አቤቱታዎችን መመሪያ ይሰራል። ይህን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይገኛል http://www.google.com/tm_complaint.html።</p> <p><strong>16. ማስታወቂያዎች</strong></p> <p>16.1 የተወሰኑ አገልግሎቶች ከማስታወቂያዎች በሚገኝ ገቢ ስለሚደገፉ ማስታወቂያዎች እና የማስታወቂያ ስራዎች ሊያሳያ ይችላሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች በአገልግሎቶቹ ውስጥ የተቀመጠ መረጃ ይዘት፣ በአገልግሎቶቹ በኩል የተሰሩ ጥያቄዎች ወይም ሌላ መረጃ ላይ ያተኮሩ ሊሆን ይችላሉ።</p> <p>16.2 Google ምንም ሳያሳውቅዎት በአገልግሎቶቹ ላይ የማስተዋወቂያ መንገድ፣ ሰልት ወይም ስፋት ለለወጥ የተመለከቱ ናቸው።</p> <p>16.3 Google አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና አገልግሎቶቹን እንዲጠቀሙ በሰጠዎት ፍቃድ መሰረት Google በአገልግሎቶቹ ላይ እንደዚህ ያሉ ማስታወቂያዎች ሊያኖር እንደሚችል ተስማምተዋል። </p> <p><strong>17. ሌላ ይዘት</strong></p> <p>17.1 ግልጋሎቶቹ ለሌላ ድረ-ገፆች ወይም ይዘት ወይም ንብረቶች የገጽ አገናኞችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ከGoogle ውጪ በሆኑ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች ለቀረቡ ማናቸውም ድረ-ገፆችን ወይም ንብረቶችን የመቆጣጠር መብት ላይኖረው ይችላል።</p> <p>17.2 Google ለእንደዚህ አይነት ውጫዊ ጣቢያዎች ወይም ንብረቶች መገኘት ኃላፊነት እንደሌለበት እና በነዚህ የድር ጣቢያዎች ወይም ንብረቶች ላይ ለሚገኙ ማንኛውም ማስታወቂያዎች፣ ምርቶች ወይም ሌላ ነገሮችን እንደማይደግፍ አረጋግጠው ተስማምተዋል።</p> <p>17.3 ርስዎ አምጠውት ሊሆን በሚችለው በእነዚህ ውጫዊ ጣቢያዎች ወይም ንብረቶች መገኘት ምክንያት፣ ወይም ርስዎ በሙሉዕነታቸው፣ በትክክለኛነታቸው፣ እዛ ለመኖራቸው እምነት በጣሉበቸው በነዚህ የድር ጣቢያዎች ወይም ንብረቶች ላይ ለሚገኙ ማንኛውም ማስታወቂያዎች፣ ምርቶች ወይም ሌላ ነገሮች ምክንያት ለሚከሰቱ ማንኛውም ጥፋቶች ወይም ጉዳቶች Google ተጠያቂ እንደማይሆን አረጋግጠው ተስማምተዋል።</p> <p><strong>18. የስምምነት ውሎች ላይ የሚደረጉ ለውጦች</strong></p> <p>18.1 Google በአለምአቀፍ የስምምነት ውሎች ወይም በተጨማሪ የስምምነት ውሎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጦችን ሊያደርግ ይችላል። እነዚህ ለውጦች ሲደረጉ፣ Google በhttp://accounts.google.com/TOS?hl=en በሚገኘው የአለምአቀፍ የስምምነት ውሎች ላይ አዲስ ቅጂ ያሰፍራል እንዲሁም ማንኛውም አዲስ ተጨማሪ የስምምነት ውሎች ይህ ለውጥ በሚነካቸው ግልጋሎቶች ውስጥ ወይም በግልጋሎቶቹ አማካያነት እንዲገኝ ይደረጋል።</p> <p>18.2 የአለምአቀፍ የስምምነት ውሎች ወይም የተጨማሪ የስምምነት ውሎች ለውጥ ከተደረገባቸው ቀን በኋላ ግልጋሎቶቹን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ Google መጠቀምዎን የተሻሻሉትን የአለምአቀፍ የስምምነት ውሎች ወይም የተጨማሪ የስምምነት ውሎች እንደተቀበሉ አድርጎ ይቆጥረዋል፣ ይህንንም ተረድተው ተስማምተዋል።</p> <p><strong>19. አጠቃላይ ህጋዊ የስምምነት ውሎች </strong></p> <p>19.1 አንዳንድ ጊዜ ግልጋሎቶቹን ሲጠቀሙ፣ (ከግልጋሎቶቹ ጋር በተገኘ ወይም በእነርሱ ምክንያት) ግልጋሎትን ሊጠቀሙ ወይም አነስተኛ ሶፍትዌር ሲያወርዱ አልያም በሌላ ግለሰብ ወይም ኩባንያ የቀረቡ ሸቀጦች ሊሸምቱ ይችላሉ። እነዚህን ግልጋሎቶች፣ ሶፍትዌር ወይም ሸቀጦች መጠቀምዎ፣ በሚመለከተው ግለሰብ ወይም ኩባንያ እና በርስዎ መካከል በተለየ የስምምነት ውሎች ተገዢ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ከሆነ፣ የስምምነት ውሎቹ ከእነዚህ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች ጋር ያለዎትን ህጋዊ ግንኙነቶች አይነኩም። </p> <p>19.2 የስምምነት ውሎቹ በርስዎና በGoogle መካከል ያለዎትን አጠቃላይ የህግ ስምምነት ይመሰርታል እንዲሁም የግልጋሎቶቹን አጠቃቀምዎን (Google በተለየ የጽሁፍ ስምምነት ለርስዎ ካቀረባቸው ከማንኛውም ግልጋሎቶች ውጪ) የሚያስተዳድሩ ይሆናል፤ በተጨማሪም ከግልጋሎቶቹ ጋር የተያያዙ በርስዎና በGoogle መካከል የተደረጉ ሁሉም ቀዳሚ ስምምነቶች ሙሉ ለሙሉ የሚተኩ ይሆናል።</p> <p>19.3 የስምምነት ውሎቹን በተመለከተ የሚደረጉ ለውጦችን ጨምሮ Google ማስወቂያውን በኢሜይል፣ በመደበኛ መልዕክት ወይም በግልጋሎቶቹ በሚላኩ ጽሁፎች ሊያቀርብልዎ እንደሚችል ተስማምተዋል። </p> <p>19.4 Google ህጋዊ መብትን ወይም በግልጋሎቶቹ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ካሳን የማይተገብር ከሆነ (ወይም Google ሊሰራ በሚችል ህግ ተጠቃሚ ከሆነ)፣ ይህ የGoogle ክፍያን የሚያስቀር መግለጫ ተደርጎ አይወሰድም እናም እነዚህ መብቶች ወይም ህጋዊ የካሳ ክፍያዎች በGoogle የሚገኙ ይሆናል። በዚህም ተስማምተዋል። </p> <p>19.5 በዚህ ጉዳይ ላይ የመወሰን ስልጣን ያለው ማንኛውም የፍርድ ቤት ህግ፣ በእነዚህም የስምምነት ውሎች የሰፈረ ማንኛውም ደንብ ልክ አለመሆኑን ከፈረደ፣ ያ ደንብ ከስምምነት የስምምነት ውሎችን በማይነካ መልኩ ከውሎቹ የሚወገድ ይሆናል። በስምምነት ውሎቹ የተካተቱት የቀሩት ደንቦች ትክክለኛ እንደሆኑ እና እንደተከበሩ የሚቀጥሉ ይሆናል።</p> <p>19.6 Google አጋር በሆናቸው ኩባንያዎች የሚገኝ እያንዳንዱ አባል ለስምምነት ውሎቹ የሶስተኛ ወገን ተጠቃሚ ይሆናል፣ እንዲሁም ሌሎች መሰል ኩባንያዎች በስምምነት ውሎቹ የሚገኝ ለእነርሱ ጥቅም የሚሰጥ (ለህጎቻቸው የሚያደላ) ማንኛውንም ደንብ፣ እንዲያስከብሩ ስልጣን ይሰጣቸዋል፤ እምነትም ይጥልባቸዋል። ከዚህ ውጪ፣ ሌላ ግለሰብ ወይም ኩባንያ ለስምምነት ውሎቹ የሶስተኛ ወገን ተጠቃሚ አይሆንም። ይህንንም በማረጋገጥ ተስማምተዋል። </p> <p>19.7 የስምምነት ውሎቹ እና በውሎቹ ስር ከGoogle ጋር ያለዎት ግንኙነት በካሊፎርኒያ ግዛት ባሉት ህጎች (የህጎቹን ደንቦች በተመለከተ ሳይጋጭ) የሚተዳደር ይሆናል። ርስዎና Google ከስምምነት ውሎቹ የወጣ ማንኛውም ህጋዊ የሆነ ጉዳይን ለመፍታት በሳንታ ክላራ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ ለሚገኘው የችሎቱ የግል ስልጣን ለማቅረብ ተስማምታችኋል። ይህም ሆኖ፣ Google አሁንም በማንኛውም ስልጣን ውስጥ የፍርድ ማገጃ ትዕዛዝ መፍትሔዎችን (ከዚህ ጋር የሚሰተካከል አስቸኳይ የህግ መፍትሔን) የመተግበር ፍቃድ ተሰጥቶታል። ይህንንም ተስማምተዋል። </p> <p><strong>20. ተጨማሪ የቅጥያዎች ስምምነት ውሎች ለGoogle Chrome</strong></p> <p>20.1 በዚህ ክፍል ያሉት እነዚህ ውሎች በርስዎ Google Chrome ቅጂ ቅጥያዎች ሲጭኑ ተግባራዊ ይሆናል። ቅጥያዎች፣ ሊሻሻሉና የGoogle Chromeን ስራ ሊያሳድጉ የሚችሉ በGoogle ወይም ሶስተኛ ወገኖች የተገነቡ አነስተኛ የሶፍትዌር ፕሮግራሞች ናቸው። ቅጥያዎች ከመደበኛ ድረ-ገፆች በበለጠ አሳሽዎን ወይም ኮምፒውተርዎን የመድረስ ልዩ መብት ሊኖራቸው ይችላል፤ የግል ውሂብዎን ማንበብና ማሻሻልንም ጨምሮ።</p> <p>20.2 ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ Google Chrome ለቅጥያዎች የሚገኙ ዝምኖችን፣ በዚህ ብቻ ያልተወሰነ ግን የስህተት መጠገኛዎችን ወይም የስራ ማሳደጊያንም ጨምሮ፣ ከሩቅ አገልጋዮች (በGoogle ወይም ሶስተኛ ወገኖች የሚስተናገዱ) ሊፈትሽ ይችላል። እነደዚህ ዓይነት ዝምኖች ለርስዎ ምንም ዓይነት ማሳወቂያ ሳይደረግ በራስ እንዲጠየቁ፣ እንዲወርዱ እንዲሁም እንዲጫኑ ተስማምተዋል።</p> <p>20.3 ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ Google የGoogle ዴቨሎፐር ስምምነት ውሎችን ወይም ህጋዊ ስምምነቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን ወይም ፖሊሲዎችን የሚጥስ ቅጥያ ሊያገኝ ይችላል። Google Chrome የእንደዚህ ዓይነት ቅጥያዎችን ዝርዝር ከGoogle አገልጋዮች በየወቅቱ ያወርዳል። Google በራሱ ውሳኔ እንደዚህ ዓይነት ቅጥያ በተጠቃሚው ስርዓት ላይ እንዳይሰራ ወይም እንዲወገድ ሊያደርግ እንደሚችል ተስማምተዋል። </p> <br> <h2>መግለጫ ሀ</h2> <p>Google Chrome በAdobe በህግ የተቋቋሙ ስርዓቶች እና በAdobe ኃላፊነቱ በአየርላንድ የተወሰነ ሶፍትዌር (በአጠቃላይ “Adobe”) የቀረቡ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ክፍሎችን ሊያካትት ይችላል። በGoogle (“Adobe ሶፍትዌር”) እንደቀረበው የAdobe ሶፍትዌር አጠቃቀምዎ ለሚከተሉት ተጨማሪ ውሎች (የ“Adobe ውሎች”)ተገዢ ይሆናል። ርስዎ፣ የAdobe ሶፍትዌርን የተቀበሉ፣ ከዚህ በኋላ “ሰብላይሰንሲ” ተብለው ይጠራሉ። </p> <p>1. የፍቃድ ገደቦች</p> <p>(ሀ) Flash Player፣ ስሪት 10.x ልክ እንደ አሳሽ plug-in ብቻ የተዘጋጀ ነው። ሰብላይሰንሲ ይህን የAdobe ሶፍትዌር ለአሳሽ plug-in በድረ-ገጽ ላይ የሚገኝ ይዘትን ደግሞ ለማጫወት እንጂ ለማንኛውም ነገር ለመጠቀም ማሻሻል ወይም ማሰራጨት ላይችል ይችላል። ለምሳሌ፣ ሰብላይሰንሲ ይህን የAdobe ሶፍትዌር ከአሳሹ ውጪ ካሉ መተግበሪያዎች (ለምሳሌ፡ ራሳቸውን ከቻሉ መተግበሪያዎች፣ መግብሮች፣ የመሳሪያ የተጠቃሚ በይነገጽ) ጋር አብሮ እንዲሰራ ለማድረግ ማሻሻል አይችልም።</p> <p>(ለ) ሰብላይሰንሲው በአንድ አሳሽ plug-in በይነገጽ በኩል እንደዚህ ያለ ቅጥያ በድረ-ገጽ ላይ ያለ ይዘትን ልክ እንደ ራሱን-የቻለ መተግበሪያ ደግሞ ለማጨወት እንዲጠቅም በማድረጊያ መንገድ የማንኛውንም Flash Player፣ ስሪት 10.x የሆነ APIs የሚያጋልጥ አይሆንም።</p> <p>(ሐ) የChrome-ማንበቢያ ሶፍትዌር የዲጂታል መብቶች አስተዳዳሪ ፕሮቶኮሎችን ወይም ከAdobe DRM ውጪ የሆኑ ስርዓቶችን የሚጠቀሙ ማንኛውንም PDF ወይም EPUB ሰነዶችን ለመተርጎሚያነት ላያገለግል ይችላል። </p> <p>(መ) ለሁሉም በAdobe DRM የተጠበቁ PDF እና EPUB ሰነዶች በChrome-ማንበቢያ ሶፍትዌር ውስጥ Adobe DRM መንቃት አለበት። </p> <p>(ሠ) የChrome-ማንበቢያ ሶፍትዌር፣ በሙያዊ ደንቦች በግልጽ ከተፈቀዱ ውጪ፣ ማንኛውም በAdobe ሶፍትዌር ውስጥ የሆኑ በAdobe የቀረቡ ችሎታዎችን ለPDF እና EPUB ቅርጸቶች እና በAdobe DRM የተደገፉትንም ጨምሮ ነገር ግን ያልተወሰኑትን ማሰናከል አይችልም። </p> <p>2. ኤሌክትሮኒክ ማስተላለፊያ። ሰብላይሰንሲው የAdobe ሶፍትዌርን ከድር ጣቢያ፣ ከኢንተርኔት፣ ከኢንትራኔት፣ ወይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ (“ኤሌክትሮኒክ ማስተላለፊያ”) ማውረድን ሲፈቅድ፣ ማንኛውንም የAdobe ሶፍትዌር በCD-ROM፣ በDVD-ROM ወይም በሌላ የማስቀመጫ መሳሪያ ያሉትን እና በኤሌክትሮኒክ ማስተላለፊያዎችን ጨምሮ በሰብላይሰንሲው የሚደረግ ማንኛውም ስርጭት በግልጽ ከተፈቀደ፣ ያልተፈቀደላቸውን ተጠቃሚዎችን ለመከልከል ለሚደረገው ምክንያታዊ የደህንነት ጥበቃ ርምጃ ተገዢ እንደሚሆን ሰብላይሰንሲው ተስማምቷል። እዚህ ላይ ከጸደቀው የኤሌክትሮኒክ ማስተላለፊያዎች ጋር የተያያዙ እና/ወይም የሰብላይሰንሲውን ውጤት ከስር ላሉ ተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የወጣ እገዳን ጨምሮ ማንኛውንም በAdobe የተዘጋጀውን ምክንያታዊ እገዳ እንደሚያስፈጽም ሰብላይሰንሲው ተስማምቷል። </p> <p>3. EULA እና የስርጭት ውሎች</p> <p>(ሀ) የAdobe ሶፍትዌር ለዋና ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ ለሰብላይሰንሲው እና ለአቅራቢዎቹ የወገነ ቢያንስ ዪከተሉትን ዝቅተኛ የስምምነት ውሎችን (የ“ዋና ተጠቃሚዎች ፍቃድ”) የያዘ ሊያስከብር የሚችል የዋና ተጠቃሚ ፈቃድ ስምምነት ስር መሆኑን ሰብላይሰንሲው ማረጋገጥ ይኖርበታል። (i) በስርጭት እና በቅጂ ላይ ያለ ክልከላ (ii) በማስተካከያዎች እና በተዋጣጡ ስራዎች ላይ ያለ ክልከላ (iii) የAdobe ሶፍትዌርን ሰው በሚገነዘበው መልክ በማሳሳት፣ ውቅረትን በመቀየር፣ በመበታተን እና ካልሆነ ደግሞ በመቀነስ ላይ ያለ ክልከላ (iv) የሰብላይሰንሲ ምርት (ልክ በንዑስ ክፍል 8 እንደተገለጸው) ባለቤትነት የሰብላይሰንሲው እና የፍቃዶቹ መሆኑን የሚጠቁሙ ደንቦች (v) የቀጥተኛ፣ ልዩ፣ የሚያጋጥም፣ የሚያስቀጣ እና ሰበባዊ ጉዳቶችን መክዳት እና (vi) በህግ በተፈቀደው ሙሉ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ (አጠቃቀሙ) ሁሉኑም የሚገበሩ መተዳደሪያ ዋስትናዎች ክህደት ቃልን ጨምሮ ሌላ የኢንዱስትሪ ደረጃ ክደት እና ገደቦች። </p> <p>(ለ) Adobe ሶፍትዌር ለስብላይሰንሲው አሰራጮች የሚሰራጨው ለስብላይሰንሲው ለአሰራጮቹ የሆነን ልክ እንደ Adobe ስምምነት ውሎች፣ Adobe እንደሚጠብቅ የስምምነት ውሎችን በያዘ የሚያስከብር የማስተላለፊያ ፍቃድ ስምምነት ስር መሆኑን ለስብላይሰንሲው ማረጋገጥ አለበት።</p> <p>4. ክፍት ሶርስ ስብላይስንሲው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ Adobe አእምሮአዊ ንብረት ወይም የባለቤትነት መብቶች ስር ያሉትን ማናኛውም መብቶች ለማንኛውም 3ኛ ወገን መስጠት ወይም እንዲሰጥ ማድረግ አይኖርበትም። ይህ ከተደረገ እንደዚህ ያለው አእምሮአዊ ንብረት ለክፍት ሶርስ (open source) ፍቃድ ወይም እቅድ የሚገዛ ይሆናል። ትርጓሜው የAdobe ሶፍትዌር የመጠቀም፣ የመሻሻል እና/ወይም የመሰራጨት ሁኔታ ያለው ወይም ሊኖረው የሚችለው ቅድመ ሁኔታ፦ (i) ለግለፅ ኮድ መልክ የወጣ ወያም የተሰራጨ (ii) የሚወጣው ስራዎችን ለመስራት ሲባል ፍቃድ የተሰጠው፤ ወይም (iii) ያለምንም ክፍያ እንደገና ሊሰራጩ የሚችሉ። አላማማዎቹን ለማብራራት ያህል ከዚህ በፊት የነበረው እገዳ ሰብላይሰንሲውን ከማሰራጨት አይከለክለውም። እንዲሁም ሰብላይሰንሲው የAdobe ሶፍትዌርን እንደ ጥራዝ ከGoogle ሶፍትዌር ጋር ያለክፍያ ማሰራጨት ይችላል።</p> <p>5. ተጨማሪ ስምምነት ውሎች። ከማንኛውም ማዘመኛ፣ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ ለሰብላይሰንሲው የቀረበ አዲስ የAdobe ሶፍትዌር ስሪቶች (በአጠቃላይ ማሻሻያዎች) ተጨማሪ የስምምነት ውሎች እና አካሄዶች እንደዚህ ላሉ የማሻሻያ እና ቀጣይ ስሪቶች ላይ እንደዚህ ያለ የእገዳ መጠን Adobe እንዲጥል የሚያስችል መብት አለው። ሰብላይስንሲው እንደዚህ ባሉ ተጨማሪ የስምምነት ውሎችና አካሄዶች ላይ ካልተስማማ ሰብላይሰንሲው ከማሸሻያ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት የፍቃድ መብት አይኖረውም። እንዲሁም ከAdobe ሶፍትዌር ጋር የስምምነት ውሎችን ለሰብላይስንሲው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ከ90 ቀናት በኃላ ወዲያው የሚቋረጥ ይሆናል። </p> <p>6. የንብረት ባለቤትነት መብት ማሳሰቢያዎች። ስብላይሰንሲው አስራጮቹ በማንኛውም መልክ ያሉ የቅጂ መብት ማስታወቂያዎችን፣ የንግድ ምልክቶችን፣ አርማዎችን ወይም ተዛማጅ ማስታወቂያዎችን፣ ወይም በAdobe ሶፍትዌር ላይ ወይም ውስጥ ሌሎች የAdobe (እና ፍቃድ ሰጪዎች፣ ሌላም ካለ) የንብረት ባለቤትነት መብቶችን ወይም አብረው ያሉ ቁሳቁሶችን እንዳይሰርዙ ወይም በማንኛውም ሁኔታ እንዳይለውጡ ይፈልጋል።</p> <p>7. ሙያዊ ቅድመ ሁኔታዎች። ሰብላይሰንሲው እና አሰራጮቹ Adobe ሶፍትዌርን ማሰራጨት እና ወይም በመሣሪያዎች ላይ ማሻሻል የሚችሉት (i) http://www.adobe.com/mobile/licensees (በዚያ ተከታይ ድረ ገጽ) የወጣውን ሙያዊ መመዘኛዎቻችንን ሲያሟሉ፣ እና (ii) Adobe ከዚህ በታች በተወሰነው መሰረት ከተረጋገጠ።</p> <p>8. ማረጋገጫ እና ማዘመን። ሰብላይሰንሲው የእያንዳንዱን መሳሪያ ነፃ መሆን ማረጋገጫ መመዘኛ የማያሟላ የAdobe ሶፍትዌር እና/ ወይም ማሻሻያ (የስብላይሰንሲው ምርት) የያዘውን የሰብላይሰንሲ ምርት (እና እያንዳንዱ የእሱ ስሪት) ከGoogle ጋር ለመግባቢያ Adobe እንዲያረጋግጥ መቅረብ ይኖርበታል። ሰብላይሰንሲው ለእያንዳንዱ ሰብላይሰንስ በ http://flashmobile.adobe.com/ ላይ የAdobe የአሁን ጊዜ የስምምነት ውሎች በወጣው የማረጋገጫ ፖኬጆች ላገኘበት አቅርቦት ይከፍላል። ማረጋገጫ ያላገኘ የሰብላይሰንሲው ምርት መሰራጨት አይችልም። ማረጋገጫ የሚካሄደው በhttp://flashmobile.adobe.com/ (ማረጋገጫ) ላይ የተገለፀው የAdobe የአሁን ጊዜ ሂደት ጋር በተያያዘ ነው። </p> <p>9. መገለጫዎች እና የመሣሪያ ማዕከል። ሰብላይሰንሲው ስለ ሰብላይሰንሲው ምርት መገለጫ ወይም እንደማረጋገጫ ሂደት አንድ ክፍል ወይም ደግሞ በሌላ ዘዴ እንዲያስገባ ሊበረታታ ይችላል። እናም ሰብላይሰንሲው እንደዚህ ያለን መረጃ ለAdobe ያቀርባል። Adobe ምናልባት፦ (i) እንደዚህ ያለን መገለጫ እንደ ምክንያታዊነቱ ወይም እንደአስፈላጊነቱ የሰብላይሰንሲውን ምርት ለማረጋገጥ ይጠቀምበታል (እንደዚህ ያሉ ምርቶችን ለማረጋገጫ የተገለበጠ ከሆነ) እና (ii) እንደዚህ ያለውን መገለጫ በhttps://devices.adobe.com/partnerportal/ ላይ (በAdobe መሣሪያ ብቃት ማረጋገጫ ስርዓት) እንዲታይ እና አሻሻዮችና የዋና ተጠቃሚዎች ይዘት ወይም ተባባሪዎች በሰብላይሰንሲው ምርት ላይ እንዴት ማየት (ለምሳሌ፣ በተወሰኑ ስልኮች ላይ የቪዲዮ ምሳሌዎች እንዴት) እንደሚቻል በAdobe ፀሀፊነት እና የማሻሻያ መንገዶች እና አገልግሎቶች እንዲገኝ ማድረግ። </p> <p>10. ወደ ውጪ መላክ። ስብላይሰንሲው የዩናይትድ ስቴትስ ህግና መተዳደሪያዎች መሰረታቸው ዩናይትድ ስቴትስ የሆኑ Adobe ሶፍትዌር ሊያካትት የሚችሉ ዕቃዎች እና ሙያዊ ውሂብ ከመላክ እና እንደገና ከመላክ የሚያግድ መሆኑን ተቀብሏል። ሰብላይሰንሲው ቢያንስ አንድ ከሆነ ተዛማጅነት ካለው የዩናይትድ ስቴትስ ወይም የውጪ መንግስት ፍቃድ ውጪ መላክ ወይም እንደገና መላክ እንደማይችል ተስማምቷል። </p> <p>11. . የቴክኖሎጂ መተላለፊያ የስምምነት ውሎች፦ </p> <p>(ሀ) ከሚተገበሩ ክፍሎች የሚተገበር ፍቃድ ወይም ስምምነት ፍለጋ ካለሆነ በስተቀር ስብላይሰንሲው የAdobe ሶትዌርን ድምፃዊ የmp3 ውሂብን መደበኛ ኮምፒውተር ባልሆኑ ላይ (ለምሳሌ፦ - ተንቀሳቃሽ ወይም set-top box) ለማስቀመጥ (encoders) ወይም ለመተርጎሚያዎች (decoders) ወይም Adobe ሶፍትዌር የmp3 መፃፊያዎች (encoders) ወይም መተርጎሚያዎች (decoders) ከAdobe ሶፍትዌር ውጪ ባሉ ማንኛውም ምርቶች እንዲጠቀሙ ወይም እንዲያገኙ በማድረግ መጠቀምም ሆነ እንዲጠቀሙ ማድረግ/መፍቀድ የለበትም። የAdobe ሶፍትዌርን በswf ወይም flv ፋይል ያሉ ቪዲዮ፣ ስዕል ወይም ሌላ ውሂብ ሊይዝ የሚችሉትን mp3 ውሂብ ለመፃፍ (encode) ወይም ለመተርጎም (decode) መጠቀሚያ ሊሆን ይችላል። ሰብላይሰንሲው በዚህ ንዑስ ክፍል በተገለፀው ክልከላ መሠረት የAdobe ሶፍትዌር መደበኛ ኮምፒውተር ባልሆኑ መሣሪያዎች ላይ መጠቀም ከmp3 ቴክኖሎጂ ጋር የተያያዘ የአእምሮዋዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ለሚኖራቸው ሶስተኛ ወገኖች ለፍቃድ የሚከፈል ሰብላይሰንሲው አእምሮዋዊ ንብረት ባለቤትነት መብቶች ለያዘው ሶስተኛ ወገን ለዚህ አይነት አጠቃቀም የሚሆን ማንኛውም ክፍያ ወይም ሌላ መጠን እዳልተከፈሉ ተቀብሏል። ለእንደዚህ ላለው አጠቃቀም ስብላይሰንሲው የmp3 መፃፊያዎች ወይም ተርጓሚዎች ከፈለገ ሰብላይንሲው ማንኛውንም የሚተገብሩ ዕውቅና ያላቸው መብቶችን ጨምሮ አስፈላጊ የአእምሮአዊ ንብረት ባለቤት ፍቃዶችን የማግኘት ኃላፊነት አለበት።</p> <p>(ለ) ሰብላይሰንሲው መጠቀም፣ መቅዳት፣ እንደገና ማባዛት እና ማስተካከል የማይችለው (i) የO2 ሶርስ ኮድን (እዚህ ላይ እንደቀረበው የሶርስ ኮዶች ክፍል) እንደ አስፈላጊነቱ የAdobe ሶፍትዌር ቪዲዮ በFlash ቪዲዮ ፋይል መልክ (.flv ወይም .f4v) እንዲሰራ ለመገልበጥ (decode)፣ እና (ii) የሰሬንሰን ስፖርክ የሶርስ ከድን (እነዚህ ላይ እንደ ሶርስ ኮድ አብሮ የቀረበው) የተወሰነ የAdobe ሶፍትዌርን ስህተት ማስተካከያ እና ብቃትን ማሳደጊያ አላማ ስላላቸው ስራዎች ነው። ከAdobe ሶፍትዌር ጋር የቀረቡ ሁሉም ከዴኮች እንደተዋቀሩ የAdobe ሶፍትዌር ክፍሎች ብቻ መጠቀም እና ማሰራጨት ወይም ሌላ የGoogle መተግበሪያዎችን ጨምሮ ለሌላ ማንኛውም መተግበሪያዎች እንዳይገኝ ማድረግ ይችላል።</p> <p>(ሐ) ሶርስ ከድ ከAAC ኮዴክ እና/ ወይም HE-AAC ከዴክ (የAAC ከዴክ) ጋር ሊቀርብ ይችላል። AAC ኮዴክን የመጠቀም ሁኔታ በሰብላይሰንሲው ለመጨረሻ ምርቶች ወይም AAC ከዴክን ለሚጠቀሙ በ VIA ፍቃድ የቀረቡ አስፈላጊ መብቶችን የሚያጠቃልለውን ትክክለኛ የመብት ፈቃድ መያዝ ጋር ይወሰናል። Adobe በዚህ ስምምነት ስር የAAC ኮዴክን ፍቃድ መብት ለሰብላይሰንሲውም ሆነ ለሰብላይሰንሲው እንደማይሰጥ ሰብላይሰንሲው በመቀበል ተስማምቷል።</p> <p>(መ) ሶርስ ኮድ በAVC የዕውቅና ፖርትፎሊዮ ፍቃድ ስር ያለ ኮድ ሊይዝ የሚችለው ተጠቃሚው በግል የንግድ ያልሆነ ጥቅሞችን (i) ቪዲዮ ከAVC መተዳደሪያዎች (AVC ቪዲዮዎች) ጋር በመስማማት እንዲፅፍ (ENCODE) እና/ወይም፣ (ii) ለግል ንግድ ያልሆነ እንቅስቃሴው ውስጥ የገባው ተጠቃሚ እና/ወይም ከቪዲዮ አቅራቢዎች AVC ቪዲዮ እንዲያቀርብ ፍቃድ ያገኘው AVC ቪዲዮ የተፃፈውን (ENCODE) AVC ቪዲዮ እንዲተረጉም (DECODE) እንዲጠቀም ያደርገዋል። በሌላ ማንኛውም ጥቅም ምንም ፍቃድ አይሰጥም ዋም አይመለከትም። ተጨማሪ መረጃ ከMPEG LA, L.L.C. See http://www.mpegla.com ማግኘት ይቻላል።</p> <p>12. ማዘመኛ። ሰብላይሰንሲው የAdobe ሶፍትዌር በሁሉም የሰብላይሰንሲው ምርቶች የAdobe ሶፍትዌር እንደ ጥራዝ ከGoogle (የሰብላይሰንሲው ምርቶች) ወይም የAdobe ጥረት በዘዴ ማለፍ አይችልም።</p> <p>13. የመለያ እና የንብረት ባለቤትነት ማስታወቂያዎች። ስብላይሰንሲው የAdobe ሶፍትዌር በህዝብ እንዲገኝ የሰብላይሰንሲው ምርት መመሪያዎች እና በሰብላይሰንሲው ምርት ፓኬጅ ወይም በሰብላይሰንሲው ምርት በተያዙ የሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ምርቶች ጋር በዘላቂ ሁኔታ የሚቆይ የንግድ ምልክት ለገበያ በሚቀርቡ ቁሳቁሶች ላይ የሚካተቱ የAdobe ሶፍትዌር የንግድ ምልክት (በትክክል የAdobe አጋር አርማን ሳያካትት) መዘርዘር አለበት። </p> <p>14. ዋስትና የለም። የAdobe ሶፍትዌር ለሰብላይሰንሲው የቀረበው ለመጠቀምሚያና ‹‹እንዳለ›› እንደገና እንዲመረት ሲሆን Adobe እና አቅራቢዎቹ የAdobe ሶፍትዌር ብቃት ወይም እሱን በመጠቀም የተገኙ ውጤቶች ላይ ዋስትና አይሰጥም እንዱሁም እይችልም። ሰብላይሰንሲው Adobeን በመወከል ምንም ዋስትና ፣ ገልፃ እና ጥቆማ እዳማይሰጥ ሰብላይሰንሲው ተስማምቷል። ስብላይሰንሲው ADOBEን ወክሎ ምንም አይንት ዋስትና ዋራንቲ እንደማያቀረብ ይስማማል።</p> <p>15. ውስንነት እና ኃላፊነት። Adobe ወይም አቅራቢዎቹ በምንም አጋጣሚ ለማንኛውም ጉዳት፣ ማንኛውም አይነት ይግባኝ ወይም ክፍያ ማንኛውም፣ ምክንያት፣ ቀጥተኛ ያልሆነ ወይም የክስተት ጉዳቶች፣ ማንኛውም ትርፍ ወይም ተቀማጭ ጥፋት፣ የAdobe ተወካይ እንደዚህ አይነት ጥፋቶች ሊደርሱ እንደሚችሉ ምክር ተሰጥቶት ቢሆንም እንኳን፣ ጉዳቶች፣ ይግባኝ ወይም ክፍያ በማንኛውም ሶስተኛ ወገን ይግባኝ ቢጠየቅም ለሰብላይሰንሲው ሃላፊነት አይወስድም። ከዚህ በፊት የነበሩ ገደቦች እና ደንቦች በሰብላይሰንሲው ስልጣን በሚተገበር ህግ በተፈቀደው መጠን የሚተገበር ይሆናል። ይሆናል።የAdobe እና የአቅራቢዎቹ ሃላፊነት ከዚህ ስምምነት ስር ወይም በተያያዘ በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ሺ ዶላሮች (የአሜሪካ $1,000.00) የተገደበ ይሆናል። በዚህ በተያዘው ስምምነት ውስጥ በAdobe ችልተኝነት በመጣ ሞት እና የአካል ቁስለት ወይም በመዋሸት(በማጭበርበር) ወንጀል ክስተት Adobe ለሰብላይሰንሲው የሚውስነውን ሃላፊነት ምንም ነገር አይገድበውም። Adobe አቅራቢዎቹን በመወከል ለሌላ ለምንም ትኩረት እና አላማ ሳይሆን የይግባኝን፣ የግዴታዎችን እገዳ ወይም/እና፣ በዚህ ስምምነት በቀረበው መሠረት ዋሰትናዎችን እና ሃላፊነትን አላማው በማድረግ እየፈፀመ ይገኛል።</p> <p>16. የይዘት መከላከያ ውሎች</p> <p>(ሀ) ፍቺዎች</p> <p>“የታዛዥነት እና የጥንካሬ መመሪያዎች” ማለት በhttp://www.adobe.com/mobile/licensees ወይም እዚህ ባለው ተከታይ ድረ-ገፅ ላይ ከተመለከተው ጀምሮ ለAdobe ሶፍትዌር የሆኑ የተዛዥነት እና ጠንካሬ መመሪያዎች የተቀናጀ ሰነድ ነው።</p> <p>«የይዘት መካላከያ ጥቅሞች» ማለት የታዛዥነት እና የጥንካሬ መመሪያዎች Adobe ሶፍትዌርን በተመለከተ እንደተሟሉ ለማረጋገጥ የተበጀ እና የAdobe ሶፍትዌርን ተጠቃሚዎች ፍጆታ ለማሟላት የተሰራጨውን ዲጂታል ይዘት በሚመለከት እንደገና ማጫወት፣ መቅዳት፣ ማስተካከል፣ እንደገና ማባዛት ወይም ሌላ እርምጃዎች በእነደዚህ ባሉ ዲጂታል ይዘት ባለቤቶች ወይም ፍቃድ ባላቸው አሰራጮች ሳይፈቀድ እንደዚህ ያሉ እርምጃዎችን መከላከል ነው።</p> <p>«የይዘት መከላከያ ኮድ» ማለት በAdobe ሶፍትዌር ውስጥ የይዘት መከላከያ ጥቅሞችን ለማስቻል ውሱን የተወከለ ስሪት ነው።</p> <p>«ቁልፍ» ማለት በAdobe ሶፍትዌር ውስጥ የተያዙ ዲጂታል ይዘትን ለመመስጠር የሚጠቅሙ ሚስጥራዊ እሴት ነው። </p> <p>(ለ) የፍቃድ እገዳዎች። የስብላይሰንሲው ከAdobe ሶፍትዌር ጋር በተያያዘ ያለውን የመለማመድ መብት ለሚከተሉት ተጨማሪ እገዳዎች እና ግዴታዎች የተጋለጠ ነው። የሰብላይሰንሲው ደንበኛ Adobe ሶፍትዌርን በተመለከተ እነዚህ ገደቦች እና ግዴታዎች ሰብላይሰንሲው ላይ በሚጥሉት ጫና ተመሳሳይ መጠን እንደሚታዘዝ ሰብላይሰንሲው ያረጋግጣል፤ የሰብላይሰንሲው ደንበኛ በእነዚህ ተጨማሪ እገዳዎች እና ግዴታዎች ላይ ታዛዥነት ቢያጎድል የሰብላይሰንሲው ቁሳቁስም ጥፋት እንዲሆነ ነው የሚቆጥረው ።</p> <p>ለ.1. ሰብላይሰንሲ እና ደንበኞች ከላይ በAdobe ውሎች በተገለጸው የማረጋገጫ ሂደት ጊዜ በሰብላይሰንሲው በጸደቀው መሰረት የተሟላ እና ጠንካራ መመሪያዎች የሚያሟሉ ብቻ የAdobe ሶፍትዌርን ማሰራጨት ይችላሉ።</p> <p>ለ.2 ሰባላይሰንሲ (i) የAdobe ሶፍትዌርን ለሚጠቁሙ በተፈቀደ ፍጆታ ዲጂታል ይዘትን ለመመስጠር ወይም የተመመሰጠረውን ለመመለስ የሚጠቅሙ የAdobe ሶፍትዌር ወይም ተዛማጅ የAdobe ሶፍትዌር ይዘት መጠበቂያ ዘዴዎችን ችግር በብልኃት ማለፍ፣ ወይም (ii) የAdobe ሶፍትዌርን ለሚጠቀሙ ፍጆታ ዲጂታል ይዘትን ለመመስጠር ወይም የተመመሰጠረውን ለመመለስ የሚጠቅሙ የAdobe ሶፍትዌር ወይም ተዛማጅ የAdobe ሶፍትዌር ይዘት መጠበቂያ ዘዴዎችን ችግር በብልኃት ለማለፍ የተበጁ ምርቶችን ማስደግ ወይም ማሰራጨት አይችልም።</p> <p>(ሐ) ከዚህ በኃላ ቁልፎቹ የAdobe አስተማማኝ መረጃን ምልክት ይወክላሉ፤ እና ከቁልፎቹ ጋር በተያያዘ ሰብላይሰንሲ Adobe ቁልፍ ኮድ አያያዝ መመሪያ (በተጠየቀ ጊዜ Adobe የሚያቀርበው) ታማኝ ይሆናል። </p> <p>(መ) ተቀያሪ የፍርድ ቤት ማገጃ ትዕዛዝ፦ የዚህ ስምምነት ጥሰት የAdobe ሶፍትዌርን ይዘት መከላከያ ወይም መጠበቂያ ዘዴዎችን ቢያጠፉና እንደዚህ ባለ ይዘት መጠበቂያ ዘዴዎች በሚተማመኑ Adobe እና የዲጂታል ይዘት ባለቤቶች ፍላጎት ላይ ልዩ የሆነና የሚቆይ ጥፋት ሊያመጣ ይችላል እና ለእንደዚህ ያለ ጥፋት በሙሉ ለማካካስ ያኛው ከገንዘብ ጋር የተያያዘው ጉዳት በቂ አይሆንም፤ ስለዚህ ሰብላይሰንሲ በተጨማሪ Adobe በእንደዚህ ያሉ ጥሰቶች የሚከሰቱ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ጨምሮ እንደዚህ ያሉ ጥፋቶችን ለመከላከል ወይም ለመገደብ Adobe ተቀያሪ የፍርድ ቤት ማገጃ ትዕዛዝ የመፈለግ ስልጣን ሊኖረው እንደሚችል ሰብላይሰንሲ ተስማምቶዋል። </p> <p>17. የታሰቡ የሶስተኛ ወገን ተጠቃሚዎች። Adobe በህግ የተቋቋመ ስርዓት እና Adobe በአየርላንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ ሶፍትዌር ከሰብላይሰንሲው ጋር የAdobe ውሎችን ጨምሮ ነገር ግን በዛ ብቻ ሳይወሰን Adobe ሶፍትዌርን በተመለከተ የታሰቡ ሶስተኛ ወገን ተጠቃሚዎች ናቸው። ሰብላይሰንሲው ምንም እንኳን ለማንኛውም ነገር ከGoogle ጋር ያለውን ስምምነት ቢቋረጥም Google የሰብላይሰንሲው የAdobe መለያ ላይዘጋ እንደሚችል እና በጽሁፍ የAdobe ውሎችን ጨምሮ ሰብላይሰንሲው ከGoogle ጋር ስምምነት ውስጥ መግባቱን ማረጋገጫ መስጠት እንደሚችል ተስማምቷል። ሰብላይሰንሲው ለእያንዳንዱ ፈቃዶች ስምምነት ሊኖረው ይገባል፤ እናም እንደነዚህ ያሉ ፍቃዶች የAdobe ሶፍትዌርን መልሶ ማሰራጨት ከተፈቀደላቸው እንደነዚህ ያሉ ስምምነቶች የAdobe ውሎችን ያጠቃለሉ ይሆናሉ።</p> <p>ኤፕሪል 12, 2010</p> </body> </html>